ፍለጋ (Chorus) አስቀድሜ ፅድቅህን አስቀድሜ ፊትህን አስቀድሜ ወደ ጏዳ አስቀድሜ በሬን ልዝጋ መጀመሪያ ፅድቅህን መጀመሪያ ፊትህን መጀመሪያ ወደ ጏዳ መጀመሪያ ላወጋህ ፍለጋ ፍለጋ ፍለጋ ቀኖቼ ይለቁ አንተን ፍለጋ x2 (Verse 1) ቆይቼ ልጥና ደጅህን ደጋግሜ ላንኳኳ በርህን የመንፈስህ ነኝ ረሀብተኛ ሰርተኸኝ በሌላ እንዳልረካ ይሄን አውቄ ነፍሴ ተሸንፋ እጅ ሰታለች እስከ ዘለአለምዋ ብትወድ በሀይለኛው ንፈስህ ብትወድ በነበልባል እሳትህ ብትወድ ዝም ባለው ፀጥታ ብትወድ በትንሽዋ ኮሽታ ብቻ አንተ ና x2 አንተ ብቻ ና x2 (Verse 2) ይሰበር አልባስጥሮሴ ከእግርህ ስር ሙሉ ማንነቴ ይጠበው እግርህን እምባዬ እንደ ውሀ ፊትህ ይፍሰስ ነፍሴ ካንተ ውጪ እኔነት የለኝም መሰውያው ላይ ይኸው አለሁኝ ብትወድ በሀይለኛው ንፈስህ ብትወድ በነበልባል እሳትህ ብትወድ ዝም ባለው ፀጥታ ብትወድ በትንሽዋ ኮሽታ ብቻ አንተ ና x2 አንተ ብቻ ና x2 (Bridge 1) አልሰለችም አንተን መጠበቅ ቀንና ለሊት አይደክመኝም እጠብቅሀለሁ ቀንና ለሊት የዘለአለም ረሀቤ ነህ የዘለአለም እርካታዬ እያረካኸኝ ምራብህ እየሞላኸኝ ምጠማህ ከጎኔ ሆነህ ምናፍቅህ እየዳስከኝ ምራብህ x2 (Bridge 2) አተረፍኩ አንተን አንተን ስላልኩ አተረፍኩ አወኩበት አንተን ስለመርትኩ አወኩበት አተረፍኩ ክብሬ ስላረኩህ አተረፍኩ አወኩበት አንተን ስለወደድኩ አወኩበት Director - Fikru Alemayehu Project Manager - AddisHiwot Feleke (Tishu) Music Arrangement - Robel Damtew Live Audio Recording - Elshadai Getahun Mixing and Mastering - Kenesa Bula Production managers - Moti Tilahun, Lielit Solomon Camera Yonas Assefa, Aser Seifu, Ephrem Abera, Mehari Haile, Eyob Tesfaye, Negasa Guteta, Moti Tilahun Bass Guitar - Beteab Kassa Lead Guitar - Kaleab Tekil, Ermiyas Taddele Drum - Mulugeta Geressu Keys - Robel Damtew, Teyent Asrat Saxophone - Nathaniel Gebretsadik Trumpet - Efrem Yasin Trombone - Kaleab Yinebeb Background Vocals - Mussie Fisseha, Ayda Abraham, AddisHiwot Feleke (Tishu), Eyerusalem Worku, Yonatan Zenebe , Solomon Bula Choir Arrangement - Solomon Bula #filega #newprotestantmezmur #hillinamusic #ethiopia #ethiopian #ethiopianmusic

protestantmezmurprotestant mezmur 2022mezmur 2023new protestant song 2023aster abebemesfin gutuazeb hailuhillina kasahunlily tilahuntekeste getinetlinurilih